Array

Health Information

 

1983-2006 . በጤና ሴክተር የታዩ ለውጦች

1. መግቢያ ፡-

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ካሉት ዘጠኝ ክልሎችና ሁለት የከተማ አስተዳደር አካባቢዎች

በስተሰሜን ምዕራብ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ ክልል ነው፡፡ ክልሉ በአባይ ወንዝ በሁለት የተከፈለ ሲሆን የክልሉ አቀማመጥ

ወጣገብ ተራራማና ከ38 ትላልቅ ወንዞች በላይ የሚገኝበት ክልል ነው፡፡ የአየሩ ፀባይ ቆላ 75% ፤ ወይናደጋ 24% እና ደጋ 1% ነው፡፡

በዚህም ምክንያት በክልሉ የከፍተኛ የሞትና የህመም ምክንያቶች ከሆኑት ወባና ሌሎች በውሃና በአካባቢ ንጽህና ጉድለት የሚተላለፉ

በሽታዎች ዋናዎቹ ናቸው ፡፡3

ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 5038 ካ.ሜ የቆዳ ስፋት ሲኖረው በሶስት ዞኖችና በሃያ ወረዳዎች የተከፋፈለ ነው፡፡

1997 ዓ.ም በተደረገው የህዝብና የቤት ቆጠራ ላይ ተመሥርቶ በተከታተይ ዓመታት በተደረገው ዓመታዊ ትንበያ መሰረት

የክልሉ ህዝብ ብዛት 755044 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 49.5% የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ 50.5% የሚሆኑት ወንዶች ናቸው ፡፡

የክልሉ ህዝብ የዕድሜ ደረጃ ክፍፍል ከአጠቃላይ ህዝብ በመቶ ሲሰላ 16.2% የሚሆኑት ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ

ያላቸው ህጻናት ሲሆኑ በአሁኑ ሰዓት የክልሉ ህዝብ ብዛት 964647 ደርሷል፡፡

ክልሉ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ ከሱዳን ፤ በደቡብ ከጋምቤላ ፤ በምሥራቅ ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልል ጋር

በመዋሰኑ ምክንያት ብዙ የህዝብ ፍልሰት ወደ ክልሉ የሚታይ ሲሆን ይህም በየጊዜው ለሚከሰቱ ወረርሽኝ በሽታዎች

መንስኤ እንደሆነ ይገመታል ፡፡ በሌላ መልኩ የህክምና ተገልጋይ ህ/ሰብ ቁጥር በየጤና ድርጅቶቹ ከመጨመሩም

በላይ በየዓመቱ ለጤና የሚመደበው የጤና በጀት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳያል ፡፡

በአጠቃላይ የክልሉ ህዝብ 90% የሚሆነው በገጠር የሚኖር ሲሆን የሚተዳደረውም በግብርና ክፍለ

ኢኮኖሚ ነው ፡፡ ጥቂት የህብረተሰቡ ክፍል በንግድ ፤ በልምድ የወርቅ ቁፋሮ እና በተለይ ከእጅ ወደ አፍ

የዕለት ሥራዎች ላይ የተሰማሩ ናቸው ፡፡ የክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገቱም የተመሰረተው በዚሁ የኃላቀር የግብርና አስተራረስ

ዘዴ ላይ በመሆኑ አብዛኛው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከባለፉት ሁለት አስር አመታት

ወዲህ ግን የገጠሩ ማህበረሰብ ከኋላ ቀር የአመራረት ዘዴ ተላቀዉ ወደ ዘመናዊ የአመራረት ዘዴ የተሸጋገሩ ሲሆን

በህክምና ዘርፍም ህብረተሰቡ በጤና ተቋማት የመገልገል ከጊዜ ወደ ጊዜ እጨመረ ይገኛል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የሚገኙበት ሲሆን በዋናነት ክልሉን የመሰረቱት

አምስት ብሔረሰቦች (በርታ ፤ ጉሙዝ ፤ ሽናሻ ፤ ማኦና ኮሞ) ይገኙበታል ፡፡ በተጨማሪም በክልሉ

የራሳቸው ቋንቋ ፤ ባህልና ወግ እንዲሁም እምነት ያላቸው ብሔር ብሔረሰቦች ይኖሩበታል ፡፡

ቤ/ጉ/ጤ/ጥ/ቢሮ በ1985 ዓ.ም መጨረሻ በአዋጅ የተቋቋመ ሲሆን የፌዴራል ጤ/ጥ/ሚ/ር አወቃቀር ፓሊሲን

መሰረት ያደረገ ነው ፡፡ በዋነኝነት የተቋቋመበት አላማ በሽታን በመከላከል ላይ ያተኮረ የጤና አገልግሎትን

በተለይም በእናቶችና ህጻናት ጤና ኘሮግራም፤ ተላላፊ በሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር፤ የወረርሽኝ

ቁጥጥር፤ የሃይጅንና አካባቢ ጤና አገልግሎት እና አስፈላጊ የፈውስ ህክምና አገልግሎት ለመስጠት ወዘተ… ላይ ልዩ

ትኩረት በመስጠት የክልሉን ህዝብ ጤና የመጠበቅና የመንከባከብ እንቅስቃሴ እየመራ ይገኛል፡፡

በጤና ፓሊሲው በግልጽ እንደተመለከተው የጤና አገልግሎት አሰጣጥ በመከላከል ላይ ያተኮረና ገጠሩን ማዕከል

ያደረገ መሰረታዊ የጤና ክብካቤ በማስፋፋት ላይ የተመሰረተ ከመሆኑም በላይ አደረጃጀቱም ለአገልግሎቱ

በሚያመች መልክ እየተደራጀ የአገልግሎት አሰጣጡ በሚያመች እና የቅብብሎሽ ስርዓትን በጠበቀ አሰራር እየተሰራ ይገኛል ፡፡

ቢሮው ይህን የጤና ፓሊሲ ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የተጣለበትን ተግባርና ሃላፊነት ለመፈጸም እንዲያስችል

የጤና ስራ አመራር ከክልል እስከ ቀበሌ በማዋቀር እና የጤና አገልግሎት ሥርዓቱንም በየደረጃው በመዘርጋት

አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ላይ ይገኛል ፡፡

} በወሊድ ዕድሜ ክልል (ከ15-49 ዓመት) ውስጥ የሚገኙ ሴቶች - 231997(24.05%)

} ነፍሰ-ጡር እናቶች - 44162(4.58%)

} ነፍሰ-ጡር ያልሆኑ ሴቶች(ከ15-49 ዓመት) – 187835(19.47%)

} ከ15 ዓመት በታች ህጻናት - 443737 (46%)

} ከ 15-59 ዓመት ዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች - 491004(50.9%)

} ከ 5 ዓመት በታች ህጻናት - 156273 (16.2%)

} በሕይወት የሚወለዱ ህጻናት - 40148 (4.16%)

} ከ 1 ዓመት በታች ህጻናት - 36629 (3.8%)

} ከ 6-59 ወራት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት - 151256 (16%)

} ከ 24-59 ወራት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ህጻናት - 99915 (10%)

} ከ 3 ዓመት በታች ህጻናት - 95699 (9%)

} አባወራ/እማወራ ብዛት - 214366( 4.5)

} 475 ቀበሌዎች ሲኖሩ - 34 የከተማ

- 441 የገጠር

} ጤ/ኬላዎች፡- አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ -376

- በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ -22

ድምር- 398(90%)

} ጤ/ጣቢያዎች፡- አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ -31

- በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ-9

ድምር- 40

} ሆስፒታሎች፡

Ø 2 አጠቃላይ ሆስፒታሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ያሉ

Ø 4 የመጀመሪያ ደረጃ ሆ/ሎች በግንባታ ሂደት ላይ ያሉ

2. ራዕይ ፤ ተልዕኮ ፤ እሴቶች ፤ ተግባርና ሃላፊነት

2.1 ራዕይ፡-

በክልሉ ጤናማ ፤ አምራች እና የበለጸገ ህ/ሰብ ተፈጥሮ ማየት

2.2 ተልዕኮ፡-

ከአጋሮቻችን ጋር በመተባበር ያልተማከለ፤ ዴሞክራሲያዊና የተቀናጀ የጤና ማበልጸግ ፤ በሽታ መከላከል ፤ ህክማናና

መልሶ ማቋቋም እንዲሁም የቁጥጥር ሥርዓት በመዘርጋት የክልላችንን ህዝቦች ከበሽታ ከሞትና ከአካል ጉዳተኝነት ማላቀቅ ፡፡

2.3 እሴቶች ፡-

· ለተገልጋይ ቅድሚያ መስጠት

· ቅንጅታዊ አሠራር

· ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት

· ለውጥ

· እምነት

· አቅምን ማጎልበት

· የፆታ እኩልነት ማረጋገጥ

2.4 ተግባርና ሃላፊነት ፡-

1. በክልሉ ውስጥ የጤና አገልግሎት እንዲስፋፋ ማድረግ፤

2. የሀገሪቱ ጤና ፓሊሲ መሠረት በማድረግ የክልሉ ህዝብ የሚጠበቅበትን ዕቅድ ኘሮግራም ማዘጋጀት፤

3. ስለህዝብ ጤና አጠባበቅ የወጡ ህጎች፤ ደንቦች፤ መመሪያዎች፤ ክልላዊ መመሪያ ያዘጋጃል ተግባራቸውን ይከታተላል፤

4. በክልሉ ውስጥ የሚቋቋሙ የመንግሥት፤ መያድና የግል ጤና ተቋማት ሆስፒታሎች፤ ጤና ጣቢያዎች፤ ክሊኒኮችና

ጤና ኬላዎች የገጠር መድሃኒት ቤቶችና መድሃኒት መደብሮች ተግባራቸውን ይከታተላል፤

5. መያዶች የግል ባለሀብቶች በጤናው ዘርፍ እንዲሳተፍ ያበረታታል የስራ ፈቃድ ይሠጣል ይህንን አስመልክቶ በሀገር

አቀፍ ደረጃ የወጡትን ደንቦች ተጠብቀው በስራ ላይ መዋላቸውን ይቆጣጠራል፤

6. የባሕል መድሃኒቶች ፍቱንነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ይቆጣጠራል፤

7. በሽታዎችን ለመከላከል ለመቆጣጠርና ለማጥፋት ክትባቶች እንዲሰጡና ሌሎች ተገቢ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል፤

8. በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ የመንግስት የጤና ተቋማት በየደረጃቸው ተፈላጊ መድሃኒቶች ዝርዝር ያዘጋጃል፤ ያቀርባል፤ ይቆጣጠራል፤

9. የሕዝብ ጤና ለመጠበቅ በሚረዳ የኳራንቲን ቁጥጥር ላይ ይሳተፋል፤

1. ስለ ስራዎች አፈጻጸም ወቅታዊ ዘገባዎች ለክልሉ መስ/ም/ቤት እና ለሚመለከታቸው ሁሉ ያቀርባል፤

2. በክልሉ የጤናና ጤና ነክ የመረጃ ስርዓት እንዲኖርና ለውሳኔ አሰጣጥ በሚያመች መልኩ ይዘረጋል፤ ይቆጣጠራል፤

3. የክልሉን የጤና ችግሮች ለመከልከል ተስማሚ የጤና አጠባበቅ ትምህርት ሥርዓቶችን ያዘጋጃል ተግባራዊነታቸውንም ይከታተላል፤

4. የሥነ-ተዋለዶ ጤና አገልግሎት እንዲስፋፋ እቅድ ያዘጋጃል፤

3. በ23 ዓመት (ከ1983-2006 ዓ.ም) የተከናወኑ ዝርዝር የጤና መርሃ-ግብሮች እና የተገኙ ለውጦች

3.1 የጤና አገልግሎት ሽፋን

በጤና ዘርፋ ትልቁ ትኩረት በመስጠት የ1ኛ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ተቌማት (Primary Health Care) የማስፋፋት ሥራ በመሥራት ሲሆን ከደርግ አሻራ በክልላችን የተገኙ ጤና ተቌማት አንድ ሆስፒታል ፤ 3 ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች ፤ እና 32 ክሊኒኮች ብቻ እንደሆኑ መረጃዎች የሚያሳዩ ሲሆን ከ1983 ዓ.ም በፊት 1 ክሊኒክ ለ10000 ህዝብ አገልገሎት ይሰጣል በሚል በወቅቱ ከላይ የተዘረዘሩትን ጤና ተቋማት በተማከለ አሰራር የጤ/ሽፋኑ ከ7.4% ያልበለጠ እንደሆነ መረዳት ይቻላል ፡፡ ጤና ቢሮ ከተቌቌመ በኃላ እስከ አሁን በተደረገው ጥረት የጤና ሽፋኑ አሁን በ88% ላይ ሲገኝ የጤና ተቋማት አደረጃጀቱ 1 ጤና ጣቢያ ለ25000 ህዝብ፤ አንድ ጀነራል ሆስፒታል ከ1-1.5 ሚሊዮን ህዝብ እና 1 ጤና ኬላ ለ5000 ህዝብ የሚገለግል ይሆናል ፡፡

3.2 ከ1983 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም የታየው የጤና ድርጅቶች ዕድገት


ተቁ

የጤና ተቌማት ዓይነት

ከ1983 ዓ.ም በፊት

እስክ 2006 ዓ/ም

ድምር

አገልግሎት በመስጠት ላይ ያለ

በመገንባት ላይ ያለ አራት የመጀመሪያ ሆስፒታል

1

ሆስፒታል

02

02

04

06

2

ጤና አጠ/ጣቢያ

03

31

09

40

3

ክሊኒክ/ጤና ኬላ/

32

389

8

397

ድምር

36 (7.4%)

409

35

444

v ከተለያዩ በሽታዎች ለመፈወስ በየጤና ድርጅቶች የሚሰጡ የህክምና አገልግሎቶች ጥራት ለማሻሻል እና ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ ሥራዎች የተሠሩ ሲሆን ጥቂቶቹ፡-

o ነባር እና አገልግሎት መስጠት የጀመሩ አዳዲስ ጤና ተቋማት እንዲያደራጃቸው የህክምና ቁሳቁሶች በፌ/ጤ/ጥ/ሚ/ር እና በቢሮ በኩል እንዲVላላቸው ተደርጎ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ያልተማከ ሥርዓት በመዘርጋት ሆስፒታሎችና ጤና አጠባበቅ ጣቢያዎች በቦርድና በማኔጅመንት ኮሚቴ እንዲተዳደሩ እና የሆስፒታል ሪፎርም እና የጤና ክብካቤ ሀብት መግኛ ሪፎርም ተግባራዊ በማድረግ ገቢያቸውን በራሳቸው ሰብስቦ መድሃኒቶችና ሎሎች የህክምና ግብአቶች በራሳቸው እንዲችሉ ተደርጓል ፡፡

o ከፍሎ መታከም የማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የነፃ ህክምና ሥርዓት ተዘርግቶላቸው እስከ 2006 በጀት ዓመት 27785 ሰዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

o እንደማንኛውም መሠረታዊ ነገሮች ህብረተሰባችን ለጤንነት በጀት የመበጀት ባህሉ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ ሲታመሙ ለመታከም እንደሚቸገር ይታወቃል፡፡ ይህን ችግር የሚቀርፍ ከሐምሌ 2000ዓ.ም ጀምሮ የኢትዩጵያ መንግሥት ማንኛውም ኢትዩጵያዊ እንደገቢው እንዲያወጣ እና እንደ ህመሙ እንዲታከም ማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ለማስጀመር በርካታ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡

o የእናቶች ሞት እና በተለያየ ድንገተኛ አደጋዎች የሚደርሰውን ሞት ለመቀነስ የበሽተኛ አላላክ ሥርዓት (Referal) መጠናከር ትልቁን ድርሻ የያዘ በመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ ለሁሉም የኢትዩጵያ ወረዳዎች አንዳንድ አቡላንስ ለማዳረስ ሀገራችን በያዘው እስትራቴጂ መሠረት በአንደኛ ዙር ለክልላችን 8 Long Base አምቡላንስ የደረሰን በመሆኑ መተዳደሪያ ደንብ በማውጣት ለ8 ወረዳዎች ተከፋፍሎ ወረዳዎቹ እስትራቴጂው ለማሳካት በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ ፡፡

o በደም እጦት ምክንያት የሚደርሰውን ሞት ለመቀነስ ወይም ለማስቀረት በክልላችን በአሶሳ ከተማ መደበኛ የደም ባንክ አገልግሎት ለመጀመር የደም ባንክ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

o በአጠቃላይ የዘመናዊ ህክምና ተጠቃሚ ህ/ሰብ እስከ 2002 ዓ.ም ባለው መረጃ ወደ 64% ያደገ ሲሆን አሁንም በከፍተኛ ደረጃ በማደግ ላይ ይገኛል፡፡

3.3 የጤና ተቋማት የህዝብ ጥምርታ የ1983 እና 2006 ዓ.ም በንጽጽር ሲታይ

ጤና ተቌም

1983 ዓ.ም

2006 ዓ.ም

ስታንዳርድ

ሆስፒታል

1፡404145

1፡1000000

1፡1000000

ጤና ጣቢያ

1፡134715

1፡25000

1፡25000

ጤና ኬላ

1፡12630

1፡5000

1፡5000

3.4 መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የሚተዳደሩ የጤና ድርጅቶች ዓይነትና ብዛት

ከ1988 ዓ.ም ወዲህ የተከፈቱ 03 መንጋሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች የመተዳደሩ ክሊኒኮች (ሆሞሻ፤ማንዱራ፤እና ያሶ በካቶሊክ) ሲገኙ በተጨማሪ በሽርቆሌ ስደተኞች ካምኘ በ’UNHCR’ የሚተዳደር አንድ (01) ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ይገኛል፡፡

3.5 የግል ጤና ድርጅቶች

. የግል ጤና ድርጅቶች የ1983 ዓ.ም ከ2006 ዓ.ም በንጽጽር ሲቀመጥ

ተ.ቁ

የጤና ድርጅት ዓይነት

1983 ዓ.ም

2006 ዓ.ም

ምርመራ

1

መካከለኛ ክሊኒክ

0

12

2

መለስተኛ ክሊኒክ

0

103

3

የመድሃኒት መደብር

0

35

4

የገጠር መድሃኒት ቤት

0

35

5

ፋርማሲ

0

02

6

ዲያግኖስቲክ ላቦላቶሪ

0

22

ድምር

209

3.6 የጤና የሰው ኃይል ልማት በሙያ ስብጥር

የጤና የሰው ኃይል ልማትን በሚመለከት የቢሮው የጤና ባለሙያዎችን የማሰልጠን አቅም እየጎለበተ የመጣ ሲሆን የባለሙያ ቁጥር ካሉት የጤና አገልግሎት መስጫ ድርጅቶች መጠንና ፍላጎት ጋር ለማጣጣም ለኘሮግራሙ ልዩ ትኩረት በመስጠት በተለያዩ ዲሲፒሊን ባለሙያዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት ከ1983 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም በክልሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ የተሰማሩትን የጤና ባለሙያዎችን ብዛትና የሙያ ስብጥር ሲታይ በጣም ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል፡፡

3.7 ጤና ጥበቃ ቢሮ ሲቋቋም እና በአሁኑ ያለውን የጤና ባለሞያዎች በንጽጽር ሲታይ

ተ.ቁ

የሙያ ዓይነት

1983

2006

1

ስፔሻሊስት ሀኪም

0

01

2

ጠቅላላ ሀኪም

02

18

3

ጤና መኮንን

01

112

4

አዋላጅ ነርስ ዲግሪና ዲፕሎማ

06

181

5

ኢንቫይሮመንታል ድግሪ

0

39

6

ኢንቫይሮመንታል ድኘሎማ

0

2

7

ላቦራቶሪ ቴክኖሎጅስት

29

8

ላብራቶሪ ቴክኒሻን

113

9

BSC ፋርማሲ

17

10

የገጠር ጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ

9ዐ6

11

የከተማ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ

0

72

12

ክልኒካል ነርስ ዲፕሎማ

0

662

13

ኢንቫይሮመንታል ድግር

0

39

14

ኢንቫይሮመንታል ድፕሎማ

0

2

15

የህብረተሰብ ጤና ድፕሎማ

0

2

16

የህብረተሰብ ጤና MSC

0

6

17

እፕድሞሎጅ

0

3

18

እስታስቲከስ

0

6

19

ሥነ-ዓዕምሮ MSC

0

3

20

ሥነ-ዓዕምሮ ዲግሪ

0

2

21

ሥነ-ዓዕምሮ MSCድፕሎማ

0

2

22

ኢፕቶ ሜትርስት ዲግሪ

0

2

23

አይን ህኪምና ዲፕሎ ማ

0

1

24

ድንገተኛ ቀዶ ህክምና

0

5

25

ባዩእስታስቲክስ

0

2

26

HIT

0

26

ድምር

1.1 የጤና ባለሙያዎች ማሰልጠኛ ተቋማት

በ1994 ዓ.ም መለስተኛ ጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ሥራውን የጀመረው የፓዌ ነርሶች ማሰልጠኛ ት/ቤት ዛሬ በዲኘሎማ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ አዲሱን የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብርን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ ማሰልጠኛ ተቋሙ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ሙሉ በሙሉ አሰልጥኖ ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም ወደ ኮሌጅ አድጎ እውቅና እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡

በተጨማሪ በክልሉ በተለያየ ዲሲፒሊን የጤና ባለሙያዎችን የሚያሰለጥኑ የግል ኮሌጆች ይገኛሉ፡፡ ይህም በክልሉ ጎልቶ የሚታየውን የጤና ባለሙያን እጥረት ችግር በመፍታት የጥራት ችግር ቢኖረውም የበኩሉን አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ሠንጠረዥ 7. የመንግሥት እና የግል ጤና ተቋማት ዝርዝር እና መጠን ጤና ቢሮ ሲቋቋም እና እስከ 2006 ዓ.ም ያለውን በንጽጽር ሲታይ ፤

ተ.ቁ

የማሰልጠኛው ዓይነት

ብዛት

የሚሰጠው የሥልጠና ደረጃ (ክሊኒካልና ፐብሊክ)

1983 ዓ.ም

2006 ዓ.ም

1

የመንግሥት ጤና ኮሌጅ

0

1

ነርስ በዲኘሎማ ፤አዋላጅ ነርስና፤የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች

2

የግል ጤና ኮሌጅ

0

01

በ10+3 (ክሊኒካል ነርስ ብቻ)

የእናቶች እና ሕጻናት ጤና አገልግሎት

በአገራችን ብሎም በክልላችን የእናቶችና ሕጻናት ህመምና ሞት ከፍተኛ በመሆኑ ይህን ለመግታት በምዕተ ዓመቱ የተቀመጡ ግብ 4 (የህጻናት ሞት በ2/3 መቀነስ -- 68/1000 በ2007 ዓ.ም ማድረስና ግብ 5 (የእናቶች ሞት በ3/4 መቀነስ-- 300/100000 በታች በ2007 ዓ.ም) በማድረስ የምዕተ-ዓመቱ ግቦች ለማሳካት የጤና ሴክተር ልማት ዕቅድ (HSDP) በመቅረጽ ከሽግግር መንግሥት በኃላ በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡

የጤና አገልግሎትና ሽፋን

ተ.ቁ

አመልካቾች

1983 ዓ/ም

በ2006 ዓ/ም

ምርመራ

1

የጤና አገልግሎት ሽፋን በመቶኛ

7

90

2

ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ሞት ምጣኔ /ከ1000/

198 (1992 ዓ.ም)

169 (2002 ዓ.ም)

3

የእናቶች ሞት ምጣኔ /100,000/

871 (1992 ዓ.ም በአገር ደረጃ)

676 (1992 ዓ.ምበአገር ደረጃ)

ስሌቱ በክልል ደረጃ አይሰራም

4

የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በመቶኛ

5%

43%

5

በሰለጠነ የጤና ባለሙያ የታገዙ ወላዶች ብዛት በመቶኛ

4%

18%

6

በወባ መከላከያ አጎበር ተጠቃሚ የሆኑ የቤተሰብ አስተዳደሪዎች በመቶኛ

-

100

7

በፀረ ወባ ኬምካል የተረጩ ቤቶቸ

1988/33883/

169300

8

የኤች አይቪ /ኤድስ ሥርጭት በመቶኛ

2.2% (በ2002 ዓ.ም

1.1% ዝቅ ብሏል

9

የቅድመ ወሊድአገልግሎት

11%

79%

10

የድህረ ወሊድ ክትትል አገልግሎት

1%

33%

11

በሰለጠነ ባለሙያ የወሊድ አገልግሎት

4%(1993) ዓ/ም

18%

12

የህፃናት ክትባት አገልግሎት ሽፋን

27% (1993) ዓ/ም

62.2

13

የነፍሰ ጡር እናቶች የኤች አይ ቪ ምክርና ምርመራ አገልግሎት ሽፋን

-

28%

14

የቲቢ ልየታ

-

45%

ከቲቢ በሽታ ሙሉ ለሙሉ የተፈወሰ

-

68%

የጤና ኤክስቴንሽ ኘሮግራም

· ይህ ኘሮግራም የጤና ሴክተር የዕድገት ኘሮግራም (HSDP) ለማስፈጸም የገጠር ህዝብ የጤና ፍላጎት ለማርካት ይቻል

· ዘንድ ሁሉም የጤና ኘሮግራም ባካተተ መልኩ 16 ፓኬጆች ተዘጋጅቶ ሁሉም አባወራዎች እና እማወራዎች የራሳቸው ጤንነት በራሳቸው እንዲያመርቱ ይቻል ዘንድ እና ሁሉንም ሞዴል እንዲሆኑ በማድረግ የምዕተ-ዓመቱ ግቦች ለማሳካት ህ/ሰቡ ከህመምና ሞት እንዲድን ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡

· ይህ ኘሮግራም በክልላችን በ1997 ዓ.ም ጀምሮ የተጀመረ ሲሆን የተፈለገውን ያህል እድገት ባያሳይም በብዙ ቀበሌዎች ለውጥ በማምጣት ከ51156 በላይ አባወራዎች በሞዴልነት እንዲመረቁ ተደርጓል፡፡ ይህ ኘሮግራም በዋነኝነት ለመተግበር ከሚያስፈልገው 886 ጤ/ኤክስቴንሽን በላይ 906 ጤ/ኤክ/ባለሙያዎች ሙሉ በሙሉ በማሰልጠን በ475 ቀበሌዎች ተሰማርተው በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪ ይህ ኘሮግራም በቅርበት እንዲከታተሉ እና እንዲገመግሙ ወደ 80 የሚጠጉ የጤና ኤክስቴንሸን ሱፐርቫይዘሮች በማሰልጠን ተስማርተዋል፡፡ እያንዳንዷ ጤና ኤክስቴንሽንም 10 በጎ ፈቃደኛ በማሰልጠን እንዲያግዟት በውስን ቀበሌዎች እንዲከናወን ተደርጓል፡፡

›. ከ1999ዓ.ም - 2006 ዓ.ም ድረስ የጤና ኤክስቴንሽን መርሀ-ግብር በተግባር ተርጉመው 16 ፓኬጆች ተግባራዊ በማድረግ የተመረቁ ሞዴል አባወራዎች ብዛት ሲታይ

ተ.ቁ

ዓ.ም

የተመረቁ

ሽፋን

1

1999

60

0.04%

2

2006

105776

49.5

ሞደል ቤተሰብ ምረቃ

የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ

የመፀዳጃ ቤት ሽፋን እስከ 2006 ዓ/ም 172796 ሲሆን ሽፋኑ 80.6% ደርሷል፡፡